በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በላስ ቬጋሱ የቴስላ ተሽከርካሪ ፍንዳታ የሞተው የአሜሪካ ወታደር ነበር ተባለ


በላስ ቬጋስ ትራምፕ ታወር መግቢያ ደጃፍ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በሥራ ላይ
በላስ ቬጋስ ትራምፕ ታወር መግቢያ ደጃፍ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በሥራ ላይ

ዩናይትድ ስቴትስ ላስ ቬጋስ ከተማ በተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሆቴል ደጃፍ በቴስላ ሳይበር ትራክ መኪና ፍንዳታ የሞተው ግለሰብ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባል ነው ብለው ባለሥልጣናት እንደሚያምኑ ተነገረ።

ይህን የተናገሩት አሶሼትድ ፕሬስ ትላንት ሐሙስ ያነጋገራቸው ሦስት የአሜሪካ ባለሥልጣናት ናቸው፡፡

ባለሥልጣናቱ ምርመራ ላይ ባለ ጉዳይ ለመናገር ሥልጣን ስላልነበራቸው ስማቸው አልተገለጸም፡፡

ሁለት የሕግ አስከባሪ ባለሥልጣናት ተሽከርካሪዋ ውስጥ የነበረው ማቲው ሊቭልስበርገር የተባለ ሰው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ሊቭልስበርገር ሰሜን ካሮላይና ውስጥ ቀድሞ ፎርት ብራግ በተባለው የጦር ሠራዊቱ የልዩ ኃይሎች መምሪያ የሚገኝበት ግዙፍ የጦር ሠፈር ያገለግል እንደነበር ሦስቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

የላስ ቬጋሱ የመኪና ፍንዳታ የተከሰተው የ42 ዓመቱ ሻምሱድ-ዲን ባህር ጃባር በአውሮፓውያኑ የዘመን መለወጫ ቀን በኒው ኦርሊየንስ 15 ሰዎችን የገደለበትን አደጋ ባደረሰበት ዕለት ነው፡፡

አደጋው የተከሰተው ኒው ኦርሊየንስ ውስጥ ፍሬንች ኳርተር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ ጃባር በፖሊስ ከመገደሉ በፊት ዐዲሱን ዓመት ለማክበር ተሰባስበው በነበሩ ሰዎች ላይ መኪናውን በፍጥነት በመንዳት ቢያንስ 15 ሰዎችን ገድሏል፡፡

ድርጊቱ በሽብር አድራጎትነት ተይዞ በመመርመር ላይ ሲሆን ፖሊስ አጥቂው ጥቃቱን የፈጸመው ብቻውን አይደለም ተብሎ እንደሚያምን ቢገልጽም የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ)

ዛሬ ሐሙስ ለጋዜጠኞ በሰጠው መግለጫ "ግለሰቡ ጥቃቱን የፈጸመው ብቻውን ነው" ብሏል፡፡ “ጥቃቱን የፈጸመው በእስላማዊ መንግሥት ሽብርተኞች ተገፋፍቶ ነው” ሲልም አክሏል፡፡

የአሜሪካ ጦር ሠራዊት አባል የሆነው ጃባርም በፎርት ብራግ የጦር ሠፈር ያገለገለ ቢሆንም አንድ ላይ አለመስራታቸውን አንደኛው ባለሥልጣን ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG