የዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት አፈጉባዔ ማይክ ጆንሰን የሪፐብሊካን መሪነት ሥልጣናቸውን ለማስጠበቅ እየታገሉ ባሉበት ወቅት፣ ከተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ድጋፍ አግኝተዋል።
ትራምፕ ሰኞ ዕለት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ ጆንሰን "ጥሩ፣ ታታሪ እና ኃይማኖተኛ ናቸው" ያሉ ሲሆን፣ ሉዚያናን ወክለው የተመረጡት ሪፐብሊካን "ትክክለኛውን ነገር ያደርጋሉ፣ እኛም ማሸነፋችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።
ትራምፕ በጽሑፋቸው "ማይክ ሙሉ ለሙሉ፣ የእኔ አጠቃላይ ድጋፍ አለው" ሲሉ አስፍረዋል።
ጆንሰን የመሪነት ሥልጣናቸው ጥያቄ ውስጥ የወደቀው፣ ከገና በፊት የመንግሥት ተቋማትን የመዘጋት አደጋ ውስጥ በጣለው የፌደራል በጀት እቅድ ዙሪያ አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ ነው።
ምንም እንኳን በበጀቱ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ ቢቻልም፣ አለመግባባቱ ጆንሰን ያላቸው ተፅእኖ የተገደበ መኾኑን እና በፓርቲያቸው ባላቸው ድጋፍም ክፍተት መኖሩን አሳይቷል ተብሏል።
ከአንድ ወር በኋላ ቃለ መሃላ ፈፅመው ሥልጣን የሚረከቡት ትራምፕ፣ በመንግሥት ላይ የተቀመጠው የዕዳ ጣሪያ እንዲነሳ መጠየቃቸውን ተከትሎ፣ አፈጉባዔው ያቀረቧቸው ሁለት የበጀት እቅዶች ውድቅ ተደርገው ነበር።
ከትራምፕ ጋራ ያላቸውን ቅርበት ለማጠናከር ጠንክረው የሠሩት ጆንሰን፣ ተመራጩ ፕሬዝዳንት የዕዳ ጣሪያውን ከፍ ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት እ.አ.አ በ2025 እንደሚያሟሉ ለማሳመን መቻላቸውም ተመልክቷል።
መድረክ / ፎረም