የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን "አሳዛኝ ክስተት" ሲሉ ለገለጹት በካዛክስታን 38 ሰዎች ለሞቱበት ለአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ የአዘርባጃኑ አቻቸውን ዛሬ ቅዳሜ በስልክ ይቅርታ ጠይቀዋል።
ክሪምሊን በመግለጫው ባለፈው ረቡዕ አውሮፕላኑ ለማረፍ በሚሞክርበት ወቅት የሩሲያ ግዛት በሆነችው በቼቺኒያ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ግሮዝኒ አቅራቢያ የሚገኙ የአየር መከላከያ መሳሪያዎች ወደ ዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ይተኩሱ እንደነበር ተንናግረዋል፡፡
አውሮፕላኑ ተመቶ የወደቀው በሩሲያ አየር መከላከያ ነው ግን አላሉም፡፡
የስልክ ልውውጡን አስመልክቶ ከክሬምሊን የተገኘው መግለጫ እንዳመለከተው ፑቲን የአዘርባጃኑን ፕሬዚዳንት ኢልሃም አሊዬቭን “አሳዛኙ ክስተት በሩሲያ የአየር ክልል ውስጥ በመፈጠሩ ይቅርታ ጠይቀዋል።” ብሏል፡፡
አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ከአዘርባጃን ዋና ከተማ ከባኩ ወደ ግሮዝኒ በመብረር ላይ እያለ ወደ ካዛኪስታን ዞሮ ለማረፍ ሲሞክር ነበር።
ከአደጋው በሕይወት የተረፉ 29 ሰዎች እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡
ትላንት አርብ የአሜሪካ ባለሥልጣን እና የአዘርባጃን ሚኒስትር በየፊናቸው ባወጡት መግለጫ ለአውሮፕላኑ መከሰክስ "የውጭ ኃይል መሳሪያ " ሲሉ የጠሩትን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
መድረክ / ፎረም