በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ከየመን የተተኮሰ ሚሳይል ማምከኗን አስታወቀች


የመን ውስጥ ጥቃት የደረሰበት የሰነዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ (ፎቶ ኤኤፍፒ)
የመን ውስጥ ጥቃት የደረሰበት የሰነዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ (ፎቶ ኤኤፍፒ)

በሁቲዎች ቁጥጥር ስር ባለችው የየመን ዋና ከተማ ሰነዓ ላይ አዲስ የአየር ጥቃት ከተፈጸመ አንድ ቀን በኋላ ዛሬ ቅዳሜ ማለዳው ላይ ከየመን የተወነጨፈ ሚሳይል አየር ላይ ማምከኑን የእስራኤል ጦር ተናግሯል።
ዛሬ ቅዳሜ “ከየመን የተተኮሰው ሚሳይል ወደ እስራኤል ግዛት ከመግባቱ በፊት ተጠልፏል " ከዚያ በፊት በኢየሩሳሌም እና በሙት ባህር አካባቢ የማስጠንቀቂያ ደወሎች ሲጮኹ ቆይተዋል። ሲል የእስራኤል ጦር አስታውቋል፡፡
ከአንድ ቀን በፊት ሰነዓ ላይ አዲስ የአየር ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን፣ ከጥቃቱ ጀርባ ያለው ማን እንደሆነ አልታወቀም፡፡ የሁቲ አማፅያን "የአሜሪካ እና የብሪታንያ ጥቃት” ነው ሲሉ ተጠያቂ አድርገዋቸዋል፡፡
ከእስራኤል ከዩናይትድ ስቴትስም ሆነ ከብሪታኒያ ጥቃቱን አስመልክቶ የተሰጠ አስተያየት የለም፡፡
በሰነዓ አውሮፕላን ማረፊያ እና በአቅራቢያው ባሉ ተቋማት ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ በጥቃቱ አራት ሰዎች ሲሞቱ 20 ሰዎች ቆስለዋል፡፡
በኢራን የሚደገፉት ሁቲዎች እኤአ በ2014 ሰነዓን ከያዙ እና መንግስትን ካስወገዱ በኋላ ሰፊውን የየመን ክፍል ተቆጣጥረዋል።
ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር የጋዛው ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ከፍልስጤማውያን ጋር አጋር ነን የሚሉ ሁቲዎች ተከታታይ ሚሳይሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወደ እስራኤል ተኩሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG