በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ከእስራኤል ጥቃት በኋላ መዘጋቱን የጤና ኃላፊዎች ተናገሩ


.ኤ.አ. ታህሳስ 6/ 2024 አንድ ፍልስጤማዊ በሰሜን ጋዛ ሰርጥ ቤቲ ላህያ በሚገኘው በካማል አድዋን ሆስፒታል አካባቢ በደረሰ ጥቃት የተጎዳን አንድ ሰው ለማጓጓዝ ፍራሽ ተጠቅሟል። (ፎቶ ኤኤፍፒ)
.ኤ.አ. ታህሳስ 6/ 2024 አንድ ፍልስጤማዊ በሰሜን ጋዛ ሰርጥ ቤቲ ላህያ በሚገኘው በካማል አድዋን ሆስፒታል አካባቢ በደረሰ ጥቃት የተጎዳን አንድ ሰው ለማጓጓዝ ፍራሽ ተጠቅሟል። (ፎቶ ኤኤፍፒ)

የእስራኤል ወታደራዊ ሃይል በሃማስ ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የገለጹት ጥቃት በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኘውን ትልቅ ሆስፒታል ከአገልግሎት ውጭ ማድረጉን እና የሆስፒታሉን ኃላፊ (ዳይሬክተሩን) በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዓለም ጤና ድርጅት እና የጤና ባለስልጣናት ዛሬ ቅዳሜ አስታወቁ።
በከማል አድዋን ሆስፒታል ላይ የተፈፀመው ጥቃት ተቋሙን “ከጥቅም ውጭ አድርጎታል” በማለት የጋዛን ከባድ የጤና ቀውስ እያባባሰው መሆኑን የፍልስጤም ግዛት የጤና ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ኤክስ ላይ ባወጣው መግለጫ "ዛሬ ጠዋት በካማል አድዋን ሆስፒታል ላይ የተፈጸመው ጥቃት በሰሜን ጋዛ የሚገኘውን የመጨረሻውን ዋና የጤና ተቋም ከአገልግሎት ውጪ አድርጎታል። የመጀመሪያ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በጥቃቱ ወቅት የሆስፒታሉ አንዳንድ ዋና ዋና ክፍሎች በከፍተኛ ሁኔታ ተቃጥለዋል፣ ወድመዋል" ሲል አርብ ረፋድ ላይ የጀመረውን የእስራኤል ጥቃት በመጥቀስ ገልጿል።
የዓለም ጤና ድርጅት አክሎ እንዳስታወቀው ከ60 የጤና ባለሙያዎች ውስጥ 25ቱ በካባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን አንዳንዶቹም ታማሚዎች፣ በመተንፈሻ መሳሪያዎች ድጋፍ ስር በመሆን ሆስፒታል እንደሚቆዩ አስታውቋል፡፡
ከመካከለኛ እስከ ከባድ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ህሙማን ወደ ወደመውና አገልግሎት ወደማይሰጠው የኢንዶኔዥያ ሆስፒታል መዛወራቸውን ዓለም አቀፉ የጤና ወኪል ገልጾ “ ለደህንነታቸው ከፍተኛ ስጋት ያደረበት መሆኑን” አስታውቋል፡፡
“የእስራኤል ኃይሎች የሆስፒታሉን ዳይሬክተር ካማል አድዋን እና ሆሳም አቡ ሳፊያን ጨምሮ በርካታ የህክምና ባለሙያዎችን አስረዋል” ሲል የሃማስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እስሩን አስመልክቶ ከእስራኤል ባለሥልጣናት የተሰጠ አስተያየት የለም፡፡
የእስራኤል ጦር በሆስፒታሉ አካባቢ ያነጣጠረው ጥቃት የሃማስ ታጣቂዎችን በተመለከተ መረጃ ላይ በመመርኮዝ መሆኑን ገልጾ ከጥቃቱ በፊት ሲቪሎች እና ሀኪሞች አካባቢውን እንዲለቁ ሁኔታዎችን አመቻችቷል ብሏል።
ዘገባው የኤኤፍፒ ነው፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG