በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ስፔን ለመሻገር የሞከሩ ከ10ሺሕ በላይ ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጡ


ፋይል - ፍልሰተኞች ኤል ሂሮ ደሴት ላ ሬስቲንጋ ወደብ ሲደርሱ በስፔን እአአ ነሃሴ 19/2024
ፋይል - ፍልሰተኞች ኤል ሂሮ ደሴት ላ ሬስቲንጋ ወደብ ሲደርሱ በስፔን እአአ ነሃሴ 19/2024

በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈረንጆች 2024 ባሕር አቋርጠው ወደ ስፔን ለመግባት የሞከሩ ቢያንስ 10ሺሕ 457 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አንድ ጉዳዩን የሚከታተል መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም አስታውቋል።

ካለፈው ዓመት ጋራ ሲነጻጸር በ58 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየም ድርጅቱ ጠቁሟል። በአሐዙ መሠረት በቀን 30 ፍልሰተኞች ወደ ስፔን ለመሻገር ሲሞክሩ ሕይወታቸውን ያጣሉ። ይህም ከ2023 ጋራ ሲነጻጸር በ18 ጨምሯል።

ከሟቾቹ ውስጥ 1ሺሕ 538 ሕጻናትና 421 ሴቶች እንደሚገኙበት የፍልሰተኞችን ሁኔታ የሚከታተለው ‘ካሚናንዶ ፍሮንቴራስ’ አስታውቋል።

ድርጅቱ መረጃ መሰብሰብ ከጀመረበት ከእአአ አቆጣጠር 2007 ወዲህ ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበበት ዓመት መሆኑም ተነግሯል።

በወጉ ያልተሠሩ ጀልባዎች፣ አደገኛ የባሕር ላይ ሁኔታዎች እንዲሁም የነፍስ አድን አገልግሎት ሰጪዎች በቂ አቅም ስለሌላቸው ችግሩ ሊባባስ መቻሉንም ድርጅቱ ጠቁሟል።በዓመቱ 60ሺሕ 216 ፍልሰተኞች ስፔን መግባታቸው ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG