በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ከትረምፕ በዓለ ሲመት በፊት ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ተመከረ


ተመራጩ ፕሬዝደንት ትረምፕ
ተመራጩ ፕሬዝደንት ትረምፕ

ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ከዶናልድ ትረምፕ በዓለ ሲመት በፊት ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ አንዳንድ ኮሌጆች እና ዩኒቨርስቲዎች በመምከር ላይ ናቸው። ዶናልድ ትረምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው የጉዞ እገዳ መጣላቸው፣ ተቋማቱ ተመሳሳይ ርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዲያድርባቸው ማድረጉ ተመልክቷል።

ትረምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ወቅት ሰባት በሚሆኑና በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ በሆኑ ሀገራት ላይ የጉዞ እገዳ ጥለው ነበር። በአንዳንዶቹ ሀገራት ላይ የተጣለው እገዳ ኋላ ላይ ቢነሳም፣ ሌሎች ሀገራት ተጨምረውበት እስከ 15 በሚሆኑ ሀገራት ላይ የጉዞ እገዳ ተጥሎ ነበር። በዚህም 40 ሺሕ ሰዎች ወደ አሜሪካ መግቢያ ቪዛ ተከልክለዋል።

ትረምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት በትምህርት ተቋማት ተቃውሞ የሚያሰሙትን ተማሪዎች በርዕዮተ ዓለማቸው መሠረት ለይተው የቪዛ እገዳ እንደሚጥሉ አስታውቀው ነበር።

በአንዳንዶቹ ተቋማት ትምህርት የሚጀመረው ትረምፕ የሥልጣን ዘመናቸውን ከመጀመራቸው በፊት በመሆኑ ተማሪዎች ወደ አሜሪካ እንደሚመለሱ ቢታወቅም፣ የአሜሪካ ቆይታቸው በትምህርት ቪዛቸው ላይ የሚወሰን ግለሰቦች ግን ትረምፕ በዓለ ሲመታቸውን እንደ አውሮፓውያን ጥር 20 ቀን ከመፈጸማቸው በፊት ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ተመክሯል።

በ2023 - 2024 የትምህርት ዘመን፣ 1ነጥብ1 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ተማሪዎች በአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች እንደተመዘገቡ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG