በቅርቡ ነው በዩናይትድ ስቴትሱ የስሚትሶኒያን ብሔራዊ ሙዚየም ሥር ከሚገኙት 21 ሙዚየሞች አንዱ ለሆነው የዋሽንግተኑ የአፍሪቃ ሥነ ጥበብ ሙዚየም ምክትል ድሬክተር ሆነው እንዲያገግሉ የተመረጡት። ሄራን ሰረቀ ብርሃን ይባላሉ።
‘ለአፍሪቃ ሥነ ጥበብ ሥራዎች መልካም ዕድል አለ’ ብለው እንደሚያምኑ የሚናገሩት ዶ/ር ሄራን፤ ሙዚየሙ የሚያዘጋጃቸውን አውደ ትዕይንቶች የሚያስተባብር በአሕጉሪቱ ተቀማጭ የሆነ ባለ ሞያ በቀጥታ የሚሳተፍበትን ሁኔታ ጠቅሰዋል።
እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2003 እዚሁ ሙዚየም ውስጥ የታየውን በኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ ሥራዎች ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ ሃሳብ ያመነጩት ዶ/ር ሄራን፤ ለወራት በዘለቀው የጥበባት ትዕይንት የተለያዩ ኢትዮጵያ ነክ ሥራዎች በማስተባበርም ተሳትፈዋል። ከስነ ጥበብ ጋር ዝምድና ባላቸው በርካታ ሥራዎቻቸው የሚታወቁት የአፍሪቃ ታሪክ ተመራማሪ፣ በነገስታቱ ዘመን በተቀናቃኝ ወገኖች መሃከል ስለሚፈጸሙ ጋብቻዎች ለድሕረ ምረቃ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ፣ ቤተ መዘክሩን በሚመለከቱ እና ሌሎች የተዛመዱ ርዕሶች ዙሪያም ያወጋሉ።
መድረክ / ፎረም