በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ የቻይናው ፕሬዝደንት በበዓለ ሲመታቸው ላይ እንዲገኙ ጋበዙ


ፎቶ ፋይል፦ በወቅቱ ፕሬዝደንት የነበሩት ዶናልድ ትረምፕ ከቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በኦሳካ የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ላይ በተገናኙበት ወቅት በኦሳካ፣ ጃፓን፣ እአአ ሰኔ 29/2019
ፎቶ ፋይል፦ በወቅቱ ፕሬዝደንት የነበሩት ዶናልድ ትረምፕ ከቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በኦሳካ የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ላይ በተገናኙበት ወቅት በኦሳካ፣ ጃፓን፣ እአአ ሰኔ 29/2019

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ከአንድ ወር በኋላ በሚደረገው በዓለ ሲመታቸው ላይ እንዲገኙ ጋብዘዋል።

ወደ ዋይት ሃውስ ሲመለሱ ከቻይና በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ ታሪፍ እንደሚጭኑ ያስታወቁት ትረምፕ ሺ ጂንፒንግን መጋበዛቸው መልካም ምኞት ለመግለጽ ዲፕሎማሲያዊ የዘንባባ ቅርንጫፍ መላካቸውን ያሳያል ሲል አሶሲዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

መጪዋ የትረምፕ የፕሬስ ኃላፊ የሆኑት ካሮላይን ሌቪት ትረምፕ ፕሬዝደንት ሺን መጋበዛቸውን ከፎክስ ኒውስ ጋራ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ አረጋግጠዋል።

የአሜሪካ የኢኮኖሚ እና ወታደራዊ ተገዳዳሪ የሆነችው ቻይና መሪ ግብዣውን ይቀበሉ እንደሁ ወደፊት የሚታይ እንደሆነ ሌቪት ተናግረዋል።

“ግብዣው ትረምፕ አጋር ከሆኑ ሃገራት መሪዎች ጋራ ብቻ ሳይሆን፣ ከባላንጣና ተገዳዳሪ ሃገራት መሪዎችም ጋራ በግልጽ ለመነጋጋር መድረክ እንደሚከፍቱ ያሳዩበት ነው” ሲሉ መጪው የትረምፕ የፕሬስ ኃላፊ የሆኑት ካሮላይን ሌቪት ለፎክስ ኒውስ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG