በደቡብ ሱዳን ሰሜናዊ ክፍል የኮሌራ ወረርሽኝ በፍጥነት በመዛመት ላይ መሆኑን በሃገሪቱ የሚገኙ የረድኤት ሠራተኞች አስታውቀዋል።
የላይኛው የናይል ክልል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ ወር ውስጥ ቢያንስ 737 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ባወጣው መግለጫ ታውቋል።
በአንድ ወቅት የንግድ ማዕከል በነበረችውና አሁን ግን ወደ ፍልሰተኞች ከተማነት በተቀየረችው ማላካል ወረርሽኙ የከፋ እንደሆነ ታውቋል።
በጎረቤት ሱዳን ባለው ጦርነት ምክንያት የቀድሞ ነዋሪዎቿ እየተመለሱ ባሉባት ደቡብ ሱዳን ከ37 ሺሕ በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተዋል።
ሕክምና ወዲያውኑ ካልተሰጠ ሕይወት ሊቀጥፍ የሚችለውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመግታት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 280 ሺሕ በአፍ የሚሰጥ ክትባት በሃገሪቱ የከፋ ስርጭት ባለባቸው አካባቢዎች ማከፋፈሉን አስታውቋል። የንፁህ መጠጥ ውሃ አለመኖርና የንጽህና አጠባበቅ ችግር ሁኔታዎችን እንዳባባሰም ታውቋል።
መድረክ / ፎረም