በዌስት ባንክ የሚገኙ የአይሁድ ሰፋሪዎች በስፍራው በሚገኙ የፍልስጤማውያን ከተሞች ላይ ተከታታይ ጥቃት ሰንዝረው ቤቶችን ሲያቃጥሉ፣ ከእስራኤል ወታደሮች ጋርም ተጋጭተዋል።
ምን ያህል ፍልስጤማውያን ጉዳት እንደደረሰባቸው ወዲያውኑ ሊታወቅ አልቻለም።
የእስራኤል ሠራዊት እንዳለው፣ ወታደሮች ቤት ፉሪክ በተሰኘች መንደር የሚገኝና ሰፋሪዎቹ የመሰረቱት ያልተፈቀደ የእርሻ ቦታን ለማፍረስ በደረሱበት ወቅት፣ የአይሁድ ሰፋሪዎች በመንደሩ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። ሰፋሪዎቹ ፖሊሶች ላይ ድንጋይ በመወርወር ጉዳት ሲያደርሱ ወደ መንደሩ በመግባትም ንብረት አቃጥለዋል።
በእስራኤልና ሐማስ መካከል ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ በዌስት ባንክ ሰፋሪዎች የሚፈጸመው ጥቃት ጨምሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል በሌባኖስ በርካታ የድሮን እና የከባድ መሣሪያ ጥቃቶች ትላንት ማክሰኞ ብትፈጽምም ሙሉ ለሙሉ ያልተከበረው የተኩስ ማቆም ስምምነቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው ተብሏል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱን ይጥሳሉ ባሏቸው የሂዝቦላ ኢላማዎች ላይ ጠንከር ያለ ጥቃት መፈጸማቸውን እንደሚቀጥሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔተንያሁ ዝተዋል።
መድረክ / ፎረም