የአዉሮፓ ኅብረት አዲሷ ከፍተኛ ዲፕሎማት ካጃ ካላስ እና ባልደረባቸው የአዉሮፓ ምክር ቤት ኃላፊ አንቶኒዮ ኮስታ ወደ ሥልጣን በመጡ የመጀመሪያ ቀን ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ዛሬ እሁድ እለት ኪቭ ገብተዋል።
አንቶኒዮ ኮስታ ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት "ከዩክሬን ጋር እንደምንቆም ግልፅ መልዕክት ለመስጠት ነው የመጣነው ሙሉ ድጋፋችንን እንቀጥላለን" በማለት ተናግረዋል።
የአውሮፓ ህብረት አዲሱ የአመራር ቡድን ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ለሥስት ዓመታት ያህል በዘለቀው ሁለንተናዊ ትግል ኪቭን ለመደገፍ ጽኑ ሆኖ እንደሚቆይ ለማሳየት ይፈልጋል።
ይሁን እንጂ በቀጣይ የጎርጎርሳውያኑ ጥር ወር ላይ ሥልጣን የሚይዙት የዩናይትድስ ስቴትሱ መጭው ዶናልድ ትራምፕ ኪቭ አስገዳጅ የሆነ የሰላም ስምምነት እንደትቀበል ጫና ያደርጋሉ በሚል ስጋት በርትቷል።
መድረክ / ፎረም