በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ፣ የኔቶ አባልነት "የጋለውን ጦርነት ምዕራፍ " ሊያስቆም እንደሚችል ተናገሩ 


በዩክሬን 65ኛ ሜካናይዝድ ብርጌድ ፕሬስ አገልግሎት የተነሳው ምስል ላይ አንድ ተዋጊ ስሎ ኖም 2 የምድር ድሮን መሳሪያ ማብራሪያ ሲሰጥ ያሳያል ።
በዩክሬን 65ኛ ሜካናይዝድ ብርጌድ ፕሬስ አገልግሎት የተነሳው ምስል ላይ አንድ ተዋጊ ስሎ ኖም 2 የምድር ድሮን መሳሪያ ማብራሪያ ሲሰጥ ያሳያል ።

የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ቮሎድሜር ዜለንስኪ ፣ ሀገራቸው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት -ኔቶን ተቀባይነት ማግኘት ከቻለች "የጋለ ጦርነት ምዕራፍ" ሲሉ የጠሩትትን በሩሲያ የታወጀጦርነት ለማስቆም እንደሚቻል ተናገሩ።

በትናንትናው ዕለት ከስካይ ኒውስ ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዜለንስኪ የሀገሪቱ ያልተያዙ ግዛቶች በኔቶ ከለላ ስር ከዋሉ እና ህብረቱን ለመቀላቀል በቀረበው ጥሪ መሰረት የዩክሬን ዓለም አቀፍ ድንበሮች ዕውቅና ካገኙ፣ ሀገራቸው ተኩስ አቁምን ለማጤን ፍቃደኛ መሆኗን ተናግረዋል ።

በአውሮፓዊያኑ 2014 ሩሲያ የዩክሬን ግዛት የነበረችው የክራይሚያን ባሕረ ገብ መሬት በኃይል ወደ ግዛቷ ከመቀላቀሏ በተጨማሪ ፣ በየካቲት 2022 ሙሉ ወረራ በማወጅ ከአጠቃላይ የዩክሬን ግዛት 20 በመቶውን ተቆጣጥራለች።


"የጋለውን የጦርነት ምዕራፍ መቋጨት ከፈለግን ፣በእጃችን ያሉ የዩክሬን ግዛቶችን በኔቶ ጥላ ስር ማድረግ አስፈላጊ ነው" ያሉት ዘለንስኪ በሩሲያ ቁጥጥር ስር ያሉ የሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍሎች "በዲፕሎማሲያዊ መንገድ" ሊመለስ እንደሚችሉ አክለዋል።

የእሳቸው ንግግር የተሰማው ፣ የአሜሪካ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ ወረራ ከጀመረች ወዲህ ዩናይትድ ስቴትስ ዩክሬንን ለመደገፍ ያፈሰሰችውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በተመለከተ ትችት በሰነዘሩ ማግስት ነው።

ትራምፕ ዋይት ሀውስን መልሰው ከተረከቡ በኃላ በ24 ሰዓታት ውስጥ ጦርነቱን ማቆም እንደሚችሉም ገልጸዋል ። ይህ መግለጫ ዩክሬን አሁን ላይ በሩሲያ የተያዙባትን ግዛቶች አሳልፋ መስጠት እንዳለባት አመላካች ተደርጎ ተተርጉሟል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ትራምፕ የዩክሬን እና የሩስያ ልዩ መልዕክተኛ ይሆኑ ዘንድ በመከላከያ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አማካሪ ሆነው ያገለገሉትን ፣ጡረተኛውን ሌተናል ጄኔራል ኪት ኬሎግን በእጩነት አቅርበዋል ።

ኬሎግ ዩክሬናውያን ወደ ድርድር ጠረጴዛው ካልመጡ የአሜሪካ ድጋፍ እንደሚያከትም የተናገሩ ሲሆን ፣ ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ ወደ ጠረጴዛው ካልመጡ ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያዊያንን በጦርነት አውድማ ለመግደል የሚስችል ማናቸውንም ድጋፍ ለዩክሬናውያን እንደምትሰጥ ተናግረዋል።

ላለፉት በርካታ ወራት ሩሲያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያለ በመጣ ሁኔታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ ሚሳኤል እና ተንሸራታች ቦምቦችን በመጠቀም የዩክሬይን ከተሞን በኃያሉ እየደበደበች ትገኛለች። ይህም ህዝቦችን ተጎጂ ከማድረግ በተጨማሪ ፣ ቀዝቃዛው ወቅት እየተንሰራፋ በመጣባት በአሁኑ ጊዜ ለኃይል መሠረተ ልማቶች ውድመት ምክንያት ሆኗል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ሮዝሜሪ ዲካርሎ ሞስኮ እያካሄደች ያለችው በዩክሬን የኃይል መሠረተ ልማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ክረምቱን "ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከነበሩት ሁሉ በጣም የከበደ ሊያደርገው ይችላል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ዩክሬን ከሩሲያ ወረራ ጋር በምታደርገው ውጊያ የሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ደጋፊ ሆኖ የሰነበተው የዩኤስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር እና የኪየቭ አውሮፓውያን አጋሮች ፣ ሩሲያ ውስጥ ባሉ ኢላማዎች ላይ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎች ለጥቅም እንዲውሉ ከፈቀዱ ወዲህ ዩክሬን የበረታ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ጀምራለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG