በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት ጀልባዎች ሰጥመው ከ20 በላይ የሶማሊያ ፍልሰተኞች ሞቱ


የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌስ (ፎቶ ፋይል)
የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌስ (ፎቶ ፋይል)

የሶማሊያ ባለስልጣናት፣ ባለፈው ሳምንት ከ20 በላይ የሚሆኑ የሶማሊያ ፍልሰተኞች፣ በማዳጋስካር የባህር ዳርቻ በሰጠሙ ሁለት የጀልባ አደጋዎች መሞታቸውን አስታወቁ።
ፍልስተኞቹ ወደ 70 የሚጠጉ ፍልሰተኞችን በጫኑ ሁለት ጀልባዎች ይጓዙ እንደነበር ተገልጿል።
የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌስ ዛሬ እሁድ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት 22 ፍልሰተኞች ሲሞቱ 48ቱ መትረፋቸውን የማዳጋስካር ባለስልጣናት የእንደነገሯቸው አስታውቀዋል።
የተረፉትን ፍልሰተኞቹን ያዳኗቸው ኖሲ ኢራንጃ ደሴት የሚገኙ የማዳጋስካር ዓሣ አጥማጆች መሆናቸውም ተነግሯል፡፡
በሕይወት የተረፉትን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አዌስ ተናግረዋል።
ጀልባዎቹ ከየት እንደተነሱ እና የመጨረሻ መዳረሻቸውን በተመለከተ አዌስ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።
የአሜሪካ ድምፅ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት ያነጋገራቸው የምስራቅ፣ የአፍሪካ ቀንድ እና ደቡብ አፍሪካ ፍልስተኞች ቢሮ ነገሩን እንደሚያውቁ ገልጸው በጉዳዩ ላይ ከሶማሊያ ባለስልጣናት ጋር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG