የሱዳን ጦር ላለፉት አምስት ወራት በፈጥኖ ደራሹ ጦር ቁጥጥር ሥር የነበረችውና ከካርቱም በስተደቡብ የምትገኘውን ቁልፏን የሴናር ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ ሲንጃን ትላንት ቅዳሜ መቆጣጠሩን አስታወቀ፡፡
ሲንጃ ለ19 ወራት በዘለቀው ጦርነት የምስራቅ እና መካከለኛው ሱዳን አካባቢዎችን በሚያገናኝ ቁልፍ መንገድ ላይ የምትገኝ ስትራቴጅካዊ ከተማ ናት።
ሲንጃ “ከአሸባሪው ሚሊሻ ነፃ ወጥታለች” ያለው የሱዳን ጦር ሠራዊት መግለጫ ከተማዪቱ “ወደ ሀገሯ እቅፍ ተመልሳለች” ብሏል፡፡
የሠራዊቱ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃን ትላንት ቅደሜ ከካርቱም በስተሰሜን 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው ሴናር ከተማ በመሄድ ጉብኝት ማድረጋቸውንና ድሉን ማክበራቸውን በሠራዊቱ የሚመራው መንግሥት የማስታወቂያ መንግሥት ተናግረዋል፡፡
የፈጥኖ ደራሹ ጦር ባለፈው ሰኔ በሰነዘረው ድንገኛ ጥቃት የክፍለ ግዛቲቱን ሁለቱን ከተሞች መቆጣጠሩ ሲገለጽ ወደ 726ሺ ሰለማዊ ሰዎች እንደተፈናቀሉ የተባበሩት መንግስትታት ድርጅትን ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘግቧል ፡፡
መድረክ / ፎረም