በሄይቲ የወሮበሎች ጥቃትን ለመግታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው ተልእኮ ውጤት ባለማሳየቱ የሀገሪቱ ዜጎች ተስፋ እየደበዘዘ መሆኑ ተነገረ፡፡
የኬንያ ፖሊሶች የወሮበሎች ጥቃትን ለመቀልበስ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው ተልዕኮ አካል ሆነው ሄይቲ ሲደርሱ የነበረው ተስፋ ከፍተኛ እንደነበር ቢገለጽም፣ የወንበዴዎች ጥቃቶች የሀገሪቱን ዋና ከተማ እንቅስቃሴዎች ሽባ አድርገዋቸዋል፡፡
የወረበሎቹ ቡድኖች በሚያደርጓቸው የተቀናጁ ጥቃቶች 85 ከመቶ የሚሆነውን የዋና ከተማውን ክፍል በመቆጣጠር ከፍተኛ መፈናቀልና ሞት እያስከተሉ መሆኑ ተነግሯል፡፡
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ቀውስ ውስጥ ከገባችው ሄይቲ ጋር ተጋፍጠዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በዋና ከተማዋ 150 ሰዎች ሲገደሉ ወደ 20ሺ የሚሆኑት መኖሪያቸውን ለቀው ተሰደዋል፡፡
በዚህ የአውሮፓውያኑ ዓመት እስካሁን ወደ 4,500 ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡
መድረክ / ፎረም