የተባበሩት መንግስታት የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ቡድን በቴህራን ላይ ውሳኔ ካሳለፈ ጥቂት ቀናት በኋላ፣ ኢራን ስለ አወዛጋቢው የኒውክሌር መርሃ ግብር ከሶስት የአውሮፓ ኃያላን ሀገራት ጋር ፣ በመጭው ዓርብ እኤአ ኖቬምበር 29 በጄኔቭ ለመነጋገር ማቀዷን የጃፓኑ ኪዮዶ የዜና ወኪል ዛሬ እሁድ ዘግቧል፡፡
ኢራን በብሪታንያ፣ በፈረንሣይ፣ በጀርመን እና በዩናይትድ ስቴትስ ለቀረበው የውሳኔ ሃሳብ፣ የመንግስት ባለስልጣናት “የተለያዩ እርምጃዎች” በማለት የጠሩትን ፣ ዩራኒየምን የሚያበለጽጉ በርካታ አዳዲስና ዘመናዊ የማብለያ ማሽኖችን በማንቀሳቀስ ምላሽ ሰጥታለች፡፡
ኪዮዶ “የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን መንግስት ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዐለ ሲመት ከመድረሱ ከጥር ወር በፊት ለኒውክለር ውዝግብ እልባት ሊሰጥ እየፈለገ ነው” ብለዋል፡፡
አንድ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣን፣ ስብሰባው በመጪው ዓርብ እንደሚካሄድ አረጋግጠው "ቴህራን የኒውክሌር ጉዳይ ሁልጊዜም በዲፕሎማሲ መፈታት አለበት ብላ ታምናለች፣ ኢራን ከድርድር ወጥታ አታውቅም።" ብለዋል፡፡
የስዊዘርላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሪፖርቱ ለተጠቀሱት ሀገራት ጥያቄዎችን አስተላልፈዋል።
እ.ኤ.አ. በ2018 በወቅቱ የነበረው የትረምፕ አስተዳደር ኢራን እኤአ 2015 ከስድስት ኃያላን ሀገራት ጋር ገብታ ከነበረው የኒውክሌር ስምምነት በመውጣት ከባድ ማዕቀቦችን ጥሏል፡፡
በዚህ የተነሳ ቴህራን የስምምነቱን ገደብ በመጣስ፣ የዩራኒየም ክምችቶችን እንደገና በመጨመር እና በጥራት በማበልጸግ ፣ የላቀ የኒውክለር ኃይል ለማመንጨት ፈጣንና ዘመናዊ የማብለያ ማሽኖችን በመትከል የተለያዩ እምርጃዎችን ወስዳለች፡፡
ስምምነቱን ለማደስ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር እና በቴህራን መካከል የተደረገው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት አልተሳካም ፡፡ ይሁን እንጂ ትረምፕ ባለፈው መስከረም የምርጫ ቅስቀሳቸው ላይ "ስምምነት መፍጠር አለብን ምክንያቱም የሚያስከትለው ነገር የማይቻል ነው፣ ስምምነት ማድረግ ይኖርብናል" ብለዋል፡፡
መድረክ / ፎረም