በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያው ሚኒስትር ለአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከባድ ማስጠንቀቂያ ላኩ


ምስሉ በ2024ቱ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት አንድ ሰው ሃርጌሳ ውስጥ በሚገኝ ምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሲሰጡ ያሳያል።
ምስሉ በ2024ቱ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት አንድ ሰው ሃርጌሳ ውስጥ በሚገኝ ምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሲሰጡ ያሳያል።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቅርቡ በሶማሌላንድ ምርጫ ላይ አስተያየት ለሰጡ በሀገሪቱ ለሚገኙ የአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከባድ ማስጠንቀቂያ ላኩ።

አህመድ ሙአሊም ፊቂ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን ምርጫ የታዘቡ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ሶማሌላንድን እንደ አንድ የተለየ ሀገር ሳይሆን እንደ ሶማሊያ አንድ ክልል መጥራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ፊቂ በሶማሊያ የዴንማርክ አምባሳደር ስቲን ሶን አንደርሰንን በሶማሌላንድ ሃርጌሳ በነበሩበት ወቅት ስለ ሰጡት አስተያየት ለማነጋገር እንዳስጠሯቸው ገልጸዋል።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ አንደርሰን በአውሮፓዊያኑ ህዳር 19 በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲቀርቡ ተነግሯቸዋል።

የሶማሌላንድ የማስታወቂያ ሚኒስትር አሊ ሀሰን መሀመድ የፊቂን እርምጃ “ምቀኝነት” ሲሉ ተችተዋል።

አሊ ፊቂን “በሶማሊላንድ ህዝብ እድገት ምክንያት ቅናት አድሮባቸዋል” ሲል ከሰዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢ ቡድን (IEOM) በሶማሊላንድ ውስጥ ስላለው ምርጫ ያዘጋጀውን ግምገማ አትሟል።

ምርጫው የተመዘገቡ መራጮች የመምረጥ መብታቸውን መተግበር እንዲችሉ ባስቻለ በአብዛኛው የተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መከናወኑን ታዛቢዎቹ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን የምርጫ ታዛቢዎቹ በተሻለ ስልጠና ሊፈቱ የሚችሉ የአሰራር እና የአስተዳደር አለመጣጣም እንከኖችን ቢያስተውሉም ፣ ምንም አይነት ከባድ የህግ ጥሰት ወይም የምርጫ ብልሹ አሰራሮችን እንዳልተመለከቱ ተናግረዋል።

የሶማሌላንድ ምርጫ ኮሚሽን የቀደሙት ውጤቶችን ከአውሮፓዊያኑ ህዳር 21 በፊት ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG