የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ፣ እስራኤል በጋዛ ያደረሰችው ጥቃት ዘር ማጥፋት መሆኑን ለማረጋገጥ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ ።ይህ ይፋ የተደረገው ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ኢዮቤልዩ በዓል አስቀድሞ እንደሚለቀቅ ከተነገረለት አዲስ መጽሐፍ ላይ ቀድመው በወጡ ቅንጫቢ አንቀጾች ላይ ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በወሰደችው እርምጃ ጋር ተያይዞ ባለው የዘር ማጥፋት ውንጀላ ዙሪያ ማጣሪያ እንዲደረግ ሲያሳስቡ ይህ የመጀመሪያቸው ነው። በአውሮፓዊያኑ መስከረም ላይ እስራኤል በጋዛ እና ሊባኖስ ያደረሰችው ጥቃት “የሞራል ህግ የጣሰ” ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ መሆኑን እንዲሁም የእስራኤል ወታደሮች ከጦርነት ህግጋት እንተደተሻገሩ ተናግረዋል።
በሄርናን ሬይስ አልካይድ የተዘጋጀው እና ከጳጳሱ ጋር በተደረገ ቃለ ምልልስ ላይ የተመሰረተው መፅሃፍ “ተስፋ ፣ ተስፋ አይቆርጥም። መንፈሳዊ ፍኖት ወደ ተሻለ ዓለም" የሚል ርዕስ ሲኖረው ፣ ከጳጳሱ የአውሮፓዊያኑ 2025 ኢዮቤልዩ በዓለ ሲመት በፊት የፊታችን ማክሰኞ ይለቀቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን አንድ ዓመት የሚዘልቅ ኢዮቤልዩ በዓል በማስመልከት ከ30 ሚሊዮን በላይ ምዕመናንን ወደ ሮም ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
"አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት በጋዛ ውስጥ የተፈጸመው ድርጊት የዘር ማጥፋት ባህሪያት አሉት " ሲሉ ጳጳሱ መናገራቸውን ፣ የመጽሃፉን ቅንጭብ ዋቢ ያደረገው ፣ ዛሬ ለንባብ የበቃው የጣሊያን ዕለታዊ ጋዜጣ ላ ስታምፓ ዘግቧል።
"በህግ ባለሙያዎች እና በዓለም አቀፍ አካላት ከተቀረጹት ልዩ ፍቺዎች ጋር የሚስማማ መሆኑን ለማረጋገጥ በጥንቃቄ መመርመር አለብን" ሲሉም አክለዋል።
ባለፈው ዓመት ርዕሳነ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ በጋዛ ከነበሩ የእስራኤል ታጋቾች እና በጦርነቱ ውስጥ ከሚኖሩ ፍልስጤማውያን ዘመዶች ጋር በተናጥል የተገናኙ ሲሆን ፣ የቫቲካን ዲፕሎማቶች ከመጠቀም የሚታቀቧቸውን “ሽብርተኝነት” እና እንደ ፍልስጤማዊያኑ ሁሉ “የዘር ማጥፋት” የሚሉትን ቃላት በመጠቀማቸው የጋለ ክርክር ቀስቀሰዋል።
ባለፈው ሳምንት ከእስር ከተፈቱት የእስራኤል ታጋቾች ልኡካን እና ጫና ሲፈጥሩ ከቆዩ ቤተሰቦቻቸው ጋር የተገናኙት ሊቀ ጳጳሱ በቅርቡ በሚለቀቀው መጽሃፍ ላይ የኤዲቶሪያል ቁጥጥር አላቸው።
ጦርነቱ የጀመረው የታጣቂው የሃማስ ቡድን በአውሮፓዊያኑ ጥቅምት 7፣ 2023 እስራኤልን ካጠቃ በኃላ ሲሆን ፣ በወቅቱ 1,200 ሰዎች ገድሎ 250 ሰዎችን አሁንም የተወሰኑት ወደ ሚገኙበት ጋዛ አፍኖ ወስዷል ።
በጋዛ የጤና ባለስልጣናት መረጃ መሰረት ፣ የእስራኤል ዓመት የተሻገረ ወታደራዊ ዘመቻ ከ 43,000 በላይ ሰዎችን ገድሏል ። ምንም እንኳን ከሟቾቹ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ። መረጃው በሲቪሎች እና በተዋጊዎች መካከል ልዩነትን አላስቀመጠም (AP)።
መድረክ / ፎረም