በጋቦን የተከናወነው ህዝበ ውሳኔ ቀደምት ውጤቶች ፣ከተመዘገቡት 860,000 መራጮች አብዛኛው ወታደራዊ አገዛዝን የሚቋጨውን አዲስ ሕገ መንግሥት ለመደገፍ ድምጽ መስጠታቸውን የሀገሪቱ መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገባዎች አመልክተዋል።
የቅዳሜው ህገ-መንግስታዊ ህዝበ ውሳኔ ውጤት ፣ ለ60 ዓመታት በሀገሪቱ ውስጥ የቆየውን የቦንጎ ቤተሰብ ስርወ መንግስት ያስወገደውን የሽግግር ወታደራዊ መንግስት ዘመን ሊደመድም ይችላል። ይፋዊ የቆጠራ ውጤቱ በቅርቡ ይፋ ይሆናል ይጠበቃል።
ባለስልጣናት እንደሚሉት ፣ የአዲሱ ህገ መንግስት መጽደቅ ፣ በአውሮፓዊያኑ ነሐሴ 30 የጋቦን መሪዎች ካለ ደም መፋሰስ ፣ የመካከለኛው አፍሪካዊቷን ሀገር ከፖለቲካ ባርነት ነጻ እንዳረገ በሚናገሩለት መፈንቅለ መንግስት ስልጣን የተቆጣጠሩት ፣ ጄኔራል ብሪስ ክሎቴር ኦሊጊ ንጊዩሜ ከገቧቸው ዐበይት ቃል ኪዳኖች መካከል አንዱ ነው።
ሰርጌ ዜንግ አንጎ የጋቦን ዜጎች በህዝበ ውሳኔው ወቅት አዲስ ህገ-መንግስት እንዲፀድቁ የምርጫ ቅስቀሳ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲ የብሔራዊ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ናቸው።
አዲሱ ሕገ መንግሥት እንደ ቦንጎ ዘመን ሥልጣን ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍበትን ሌላኛ የፖለቲካ ሥርወ መንግሥት(ውርርስ) ማንኛውንም ዕድል እንደሚገታ ተናግረዋል።
ነገር ግን ተቃዋሚዎች እና ሲቪል ማህበረሰቦች የሕገ መንግሥቱ ረቂቅ ወታደራዊው ገዥ ጄኔራል ንጉዌማን ለፕሬዚዳንትነት እንዳይወዳደሩ መከልከል ነበረበት ብለዋል።
በወታደራዊ አመራሮች ህገ መንግስቱ የተዘጋጀው ለፕሬዚዳንቱ ከልክ ያለፈ ስልጣን ለመስጠት ፣ ንጉዌማ በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ለማድረግ እንደሆነም አክለዋል።
የጋቦን ተቃዋሚዎች እና የሲቪል ማህበራት የህዝበ ውሳኔውን ውጤት በፍርድ ቤት እንደሚቃወሙ ቢናገሩም ተጨማሪ ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም።
የጋቦን መንግስት የቅዳሜው ህዝበ ውሳኔ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ግልጽ ነበር ብሏል።
አዲሱ ህገ መንግስት ከቦንጎ የአባት እና ልጅ የስልጣን ዘመን በተለየ የግለሰቦችን ነፃነት ያስከብራል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና የመካከለኛው አፍሪካ ምጣኔ ሀብት እና የገንዘብ ማህበረሰብ ፤ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እንደተናገሩት የምርጫ ጣቢያዎች ዘግይተው በመከፈታቸው ዘግይቶ ከተጀመረው ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ምርጫው ሰላማዊ እና ግልፅነት የተሞላበት ነበር።
የህዝበ ውሳኔው ውጤት ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ፣ ጋቦን በየካቲት ወር የምርጫ ህጎቿን በማዘጋጀት ፣ የምርጫ አስተዳደር አካልን ትፈጥራለች ተብሎ ይጠበቃል ። በነሐሴ 2025 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ደግሞ ሁለት አመት ያስቆጠረውም ሽግግር ጊዜ ለመቋጨት ፕሬዚዳንታዊ፣ የፓርላማ እና የአካባቢ ምርጫዎችን ታከናውናለች።
ወታደራዊው ገዥ ንጉሜ ለወደፊቱ በሚደረጉ ምርጫዎች ላይ ዕጩ ስለመሆናቸው ይፋ ባያደርጉም በዚህ ህዝበ ውሳኔ ላይ ያለው ህገ መንግስት ግን ለፕሬዚዳንትነት ከመወዳደር አይከለክላቸውም።
መድረክ / ፎረም