በሰሜናዊ ህንድ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በአራስ ሕፃናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ አስር አዲስ የተወለዱ ሕፃናትን ሲሞቱ 16 ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
አርብ አመሻሽ ላይ በህንድ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት በጃንሲ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥየእሳት አደጋው በተከሰተበት ወቅት 55 ጨቅላ ህጻናት ህክምና እየተደረገላቸው ነበር ተብሏል፡፡
የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎችም አደጋው ከተከሰተ ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ የህይወት ማዳን ስራ መጀመራቸውንና ይህም የህይወት አድኑን ጥረት አዘግይቶታል ሲሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
በህንድ ውስጥ የእሳት ቃጠሎ የተለመደ መሆኑን የገለጸው የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ የግንባታ ህጎች እና የደህንነት ደንቦች ብዙ ጊዜ በቤት ገንቢዎች እና በነዋሪዎች ይጣሳሉ ብሏል፡፡. ይህም በሀገሪቱ ካለው ደካማ የጥገና ስርዓት እና የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እጥረት ጋር ተዳምሮ በእሳት አደጋ ለሚከሰት ሞት ምክንያት ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡
መድረክ / ፎረም