በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ደቡባዊ ቤሩትን በአየር ደበደበች 


በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ደቡባዊ ክፍል ፍንዳታ ሲከሰት የሚያሳይ፣
በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ደቡባዊ ክፍል ፍንዳታ ሲከሰት የሚያሳይ፣

የእስራኤል ጦር ሃይል ነዋሪዎች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ ካስጠነቀቀ ትንሽ ቆይታ በኋላ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ደቡባዊ ክፍል ፍንዳታ ሲከሰት የሚያሳዩ የተንቀሳቃሽ ምስሎች ወጥተዋል፡፡

የሂዝቦላ ታጣቂ ዋና ይዞታ እንደሆነ በሚነገርለት በዚህ አካባቢ እስራኤል ከማክሰኞ እለት ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሰች ይገኛል፡፡

ጥቃቱ ከመፈጸሙ ጥቂት ቀደም ብሎ የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ አቪሻይ አድራኢ በሃሬት ህሪክ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ለቀው እንዲወጡ በ X የማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ጥረ አስተላልፈው ነበር፡፡

የሊባኖስ መንግስት ብሄራዊ የዜና ወኪል (ኤን ኤን ኤ) በበኩሉ "ጠላት" ሲል በገለጻት እስራኤል በሃሬት ሂሪክ አቅራቢያ የደረሰውን ጨምሮ ሶስት የአየር ጥቃቶች ደርሰዋል ብሏል፡፡

እስራኤል በደቡባዊ ቤይሩት ላይ ተደጋጋሚ የአየር ድብደባ መፈጸሟን ተከትሎ በርካታ ንፁሀን ዜጎች ከአካባቢው እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡

ሂዝቦላ በበኩሉ በሰሜናዊ እስራኤል የሚገኘው የእግረኛ ጦር ሻለቃ ዋና መሥሪያ ቤት ላይ ያነጣጠረ ሁለት የሮኬት ጥቃቶችን ሌሊት ላይ ማድረሱን ገልጿል።

የሊባኖስ ባለስልጣናት ሂዝቦላ እና እስራኤል የተኩስ ልውውጥ ከጀመሩበት ካለፈው አመት ጥቅምት ጀምሮ ከ3,440 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሊባኖስ መንግስት መገናኛ ብዙሃን የእስራኤል የምድር ጦር ሃይሎች በሊባኖስ ውጊያ ከጀመሩ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ወደ ሊባኖስ ጠልቀው መግባታቸውንና ከሂዝቦላህ ታጣቂዎች ጋር ከፍተኛ ውጊያ ካደረጉ በኋላ እንዳፈገፈጉ ዘግበዋል።

ሪፖርቶቹ ዛሬ ጥዋት የእስራኤል ወታደሮች በደቡብ ሊባኖስ በምትገኘው ቻማ መንደር በእስራኤል ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ ስትራቴጂካዊ ኮረብታ መያዛቸውንና ቆይተው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች የቤይሩትን ደቡባዊ ሰፈሮች እና ሌሎች አካባቢዎችን እየደበደቡ ባሉበት በአሁኑ ወቅትም የሊባኖስ እና የሂዝቦላህ ባለስልጣናት ጦርነቱን ለማቆም በዩናይትድ ስቴትስ የቀረበውን ረቂቅ ሀሳብ እያጤኑት ነው ተብሏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG