በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን በእስያ ፓስፊክ የምጣኔ ሃብት ትብብር ጉባኤ ከታይዋኑ ልዑክ ጋር ተወያዩ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን በሊማ፣ ፔሩ፣ እአአ ኅዳር 14፣ 2024
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን በሊማ፣ ፔሩ፣ እአአ ኅዳር 14፣ 2024

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ሊማ ፔሩ ላይ እየተካሄደ ካለው በአገራቱ የምጣኔ ሃብት ትብብር የመሪዎች ጉባኤ አስቀድሞ በትላንትናው ዕለት ነው፤ ከታይዋኑ ልዑክ ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩት።

ብሊንከን በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ እንዳመለከቱት ውይይቱ የኢኮኖሚ ትብብሮችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

ሊማ ላይ ሊን ሂሲን-ኢ ጋር ተገናኝተን እያደገ ስለመጣው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታችን፤ እንዲሁም ግልጽ፣ ተለዋዋጭ እና ሰላማዊ የሆነ የኢንዶ-ፓሲፊክ ትብብር ለመፍጠር ያለን ዘላቂ የጋራ ቁርጠኝት ተነጋግረናል ብለዋል።

ከጉባኤው መድረክ ትይዩ የተካሄደው እና ለ20 ደቂቃዎች የዘለቀው ውይይታቸው ቀደም ሲል በብሊንከን የኦፊሴል ሥራ መርሃ ግብር ላይ ያልተገለጸ መሆኑም ተጠቁሟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG