በኢትዮጵያ የብር የመግዛት አቅም መዳከምን ተከትሎ ቋሚ ደመወዝተኞችን የኑሮ ሁኔታው እየፈተናቸው መሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ገለጸ፡፡
የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ መንግሥት የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ የኑሮ ጫናውን የሚያቃልሉ ኢኮኖሚያዊ ርምጃዎች እንዲወስድ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን በደብዳቤ መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሃብት መምህር የሆኑት ዶክተር አጥላው ዓለሙ በበኩላቸው "መንግሥት የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ ቋሚ ደመወዝተኞች ተጨማሪ ገቢ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይኖርበታል" ብለዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ከገንዘብ ሚንስቴር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ነገር ግን የገንዘብ ሚንስትር ደኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በቅርቡ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ መንግሥት የደመወዝ ጭማሪ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ጫናውን ለማቃለል እየሠራ ስለመሆኑ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡
መድረክ / ፎረም