በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በውይይት እንደሚቋጭ በመሪዎቹ መካከል ቃል መገባቱት በክልል ከሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ከተነገረ ከዐሥር ቀናት በኋላ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በእነ ዶ.ር. ደብረጽዮን የሚመራውን ቡድን “ይፋዊ መፈንቅለ መንግሥት እያካሄደ ነው” ሲል ከሷል።
አስተዳደሩ ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ በአስተዳደሩ ሥር የሚገኙት የፓርቲው አመራሮች ያለ ቅድመ ኹኔታ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለውይይት ዝግጁ መኾናቸውን ገልጿል። በመግለጫው ላይ በእነ ዶ.ር. ደብረ ጽዮን ብረሚካኤል ወገን በኩል ምላሽ ለማግኘት በስልክ እና በአካል ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ)
መድረክ / ፎረም