በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁቲዎች ወደ እስራኤል ጦር ሰፈር ሚሳይል ተኮሱ


በሊባኖስ ምሥራቃዊ መንደር፣ እስራኤል የአየር ድብደባ ባካሄደችበት ቦታ አንድ ግለሰብ ከሁለት ህፃናት ጋር በፍርስራሹ ላይ ሲራመድ - ሕዳር 11፣ 2024
በሊባኖስ ምሥራቃዊ መንደር፣ እስራኤል የአየር ድብደባ ባካሄደችበት ቦታ አንድ ግለሰብ ከሁለት ህፃናት ጋር በፍርስራሹ ላይ ሲራመድ - ሕዳር 11፣ 2024

የሁቲ አማፂያን ሰኞ እለት ከየመን ወደ እስራኤል የተኮሱት ሚሳይል እየሩሳሌም አቅራቢያ በከሸፈበት ወቅት አየር ላይ እሳት ያስነሳ ሲሆን፣ አማፂያኑ ጥቃቱን ተከትሎ ባወጡት መግለጫ በማዕከላዊ እስራኤል የተሳካ ጥቃት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል።

በኢራን የሚደገፈው ታጣቂ ቡድን ባወጣው መግለጫ "ናሃል ሶሬክ የጦር ሰፈር" ላይ ያነጣጠረ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዱን የገለጸ ሲሆን "ጥቃቱ ኢላማውን መምታቱን እና እሳት ማስነሳቱን" ገልጿል።

ሁኔታውን ተከትሎ የእስራኤል ጦር ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በላከው መግለጫ፣ ከየመን የተወነጨፈው ሚሳይል፣ ከእየሩሳሌም በስተምዕራብ በሚገኝ ቤተ ሸመሽ የተሰኘ አካባቢ የከሸፈ መሆኑን እና ይህ የፈጠረው እሳት በሰማይ ላይ መታየቱን አስታውቋል።

መግለጫው አክሎ የሁቱ ሚሳይል የእስራኤልን ግዛት ዘልቆ አለመግባቱን አመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁቲዎች የሚቆጣጠሩት የቴሌቭዥን ማሰራጫ ጣቢያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና እንግሊዝ አምራን እና ሰዓዳ በተሰኙ የየመን አካባቢዎች ላይ ያነጣጠረ ተከታታይ የአየር ድብደባ ማካሄዳቸውን አስታውቋል።

በሌላ ዜና፣ ማዕከላዊ ጋዛ ውስጥ ተፈናቃይ ቤተሰቦች ተጠልለው በሚገኙበት ድንኳን ላይ እስራኤል እሁድ እለት ባካሄደችው ጥቃት ቢያንስ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ እስራኤል እሁድ ጠዋት በሴሜናዊ ጋዛ፣ ስደተኞች ተጠልለው የሚገኙበት መጠለያ ጣቢያ ላይ ባካሄደችው የአየር ጥቃት፣ ዘጠኝ ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ 17 ሰዎች መገደላቸውን አል አህሊ የተሰኝ ሆስፒታል አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG