የትግራይ ክልልን መነሻ አድርጎ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ተስፋፍቶ የነበረውን ግጭት ያስቆመው፣ የፕሪቶሪያ ተኩስን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት ሁለተኛ ዓመትን አስመልክተው መግለጫ ያወጡት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊነክን፤ “ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደተመለሱ አድርገው መግለፃቸው ተገቢ አይደለም ሲሉ” ሦስት ፓርቲዎች ተቃውሞ አቀረቡ።
ህወሓት ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል ሥር ከነበሩትና ምዕራብ ትግራይ በሚል ከሚጠሩት አካባቢዎች የተፈናቀሉት ሰዎች እስከ አኹን ወደ ቀያቸው እንዳልተመለሱ ገልጿል።
ተፈናቃዮች ለመመለስ፣ መተማመን ለመገንባት እና በክልሉ ፀጥታ ለማስፈን በስምምነቱ መሰረት ከኢትዮጵያ መከላከያ ውጭ ያሉ ኃይሎች መውጣት ይገባቸዋል ሲል አስታውቋል።
ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የዩናይትድ ስቴት ስምምነቱ እንዲተገበር የምታደርገውን ጥረት አድንቆ፣ የችግሩን ምንጭ ተረድቶ ጵላባት ለመስጠ አስቸኳይ የፖለቲካ ውይይት ያስፈልጋል ብሏል። ሌሎች ሁለት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችም ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም