ሶማሊያ ውስጥ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በትላንት በተደረገ ከባድ ጦርነት ቢያንስ 11 የሶማሌ ክልል እና የፌደራል መንግስት ሃይሎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ጦርነቱ የተካሄደው ከጁባላንድ ግዛት ኪስማዮ በስተደቡብ ምዕራብ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዋያንታ አካባቢ የመንግስት ሃይሎች ታጣቂዎቹ ይሰባሰባሉ በተባለበት ቦታ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ ነው።
ከመገናኛ ብዙኃን ጋር መነጋገር ያልተፈቀደላቸውና ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሦስት ባለሥልጣናት፣ 11 የክልልና የመንግሥት ወታደሮች ሲገደሉ ከ20 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
በግጭቱ ከ20 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን ከባለስልጣናቱ አንዱ ተናግረዋል።
ባለፈው አመት የሶማሊያ ሃይሎች በተመሳሳይ አካባቢ ባደረጉት ዘመቻ የአልሸባብ ምክትል አሚር ነበር የተባለውን ግለሰብ መግደላቸውን የክልሉ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
አምና በአልሸባብ ታጣቂዎች ላይ በዋይንታ አካባቢ “ራስን በጋራ መከላከል” በተሰኘው የአሜሪካ ጦር የአየር ጥቃት ሶስት ተዋጊዎች ተገድለዋል።
መድረክ / ፎረም