ትላንት ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲው እጩ ዶናልድ ትረምፕ ከዲሞክራቲክ ፓርቲው ተፎካካሪያቸው ከምክትል ፕሬዚደንት ካምላ ሃሪስ ጋር ብርቱ ፉክክር አድርገው አሸንፈዋል፡፡ መጀመሪያ 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት የነበሩት ትረምፕ በመጪው ጥር ወር 47ኛው ፕሬዚደንት ሆነው በድጋሚ ኋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ይገባሉ፡፡ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ትኩረትን ስቦ የከረመው የአሜሪካ ምርጫ ውጤት በቀጣይ የሀገር ውስጥ ፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ምን አንድምታ ይኖረዋል ስትል ስመኝሽ የቆየ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራንን አነጋግራለች።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ፋይል ያገኛሉ)
መድረክ / ፎረም