ጀርመን ኢራን ኢራናዊው-ጀርመናዊውን ጃምሺድ ሻርማህድ ላይ የፈጸመችውን የሞት ቅጣት ተከትሎ በኢራን የሚገኘውን አምባሳደሯን ጠራች፡፡
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ማክሰኞ እንደለገለጸው “በርሊን በጀርመን የኢራን ጉዳይ ፈጻሚን በመጥራት ግድያውን እንደምትቃወም አስታውቃለች፡፡” ብሏል፡፡
“በኢራን አገዛዝ ድርጊት ከፍተኛ ተቃውሞአችንን ልከናል፣ ተጨማሪ እርምጃ የመውሰድ መብታችን የተጠበቀ ነው” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በማህበራዊ መድረክ ኤክስ ላይ ባወጣው ጽሁፍ ተናግሯል።
በቴህራን የሚገኙት የጀርመን አምባሳደር ወደ ኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመቅረብ የጃምሺድ ሻርማህድን ግድያ በተጠናከረ መልኩ መቃወማቸውን የገለፁ ሲሆን፣ የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ አምባሳደሩን ለምክክር ወደ በርሊን መጥራታቸው ተገልጿል፡፡
ኢራናዊው-ጀርመናዊ ጃምሺድ ሻርማህድ የሽብር ጥቃት ፈጽሟል ተብሎ ከተፈረደበት በኋላ በሞት መቀጣቱን የኢራን መንግስት መገናኛ ብዙሃን ትላንት ሰኞ ዘግበዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ የመኖሪያ ፍቃድ ያለው ሻርማህድ እኤአ በ2023 በኢራን እስላማዊ ህግጋት ውስጥ እንደ ትልቅ ወንጀል ነው በተባለውና የአምላክን ትዕዛዝ መተላለፍ በሚያመልከተው "ምድራዊ ኃጢአት" ክስ የሞት ቅጣት እንደተፈረደበት ተገልጿል፡
ሻርማህድ ኢራን ውስጥ የዘውድ ሥርዐት ደጋፊ ቡድንን በመምራት እ.ኤ.አ.በ2008 የ12 ሰዎች ሞትና 100 ሰዎች የቆሰሉበትን አደጋ ባስተከለው የቦምብ ፍንዳታ እና እንዲሁም በሀገሪቱ ውስጥ ሌሎች ጥቃቶችን በማቀድ መከሰሱ ተጠቅሷል፡፡
የሻርማህድ ሴት ልጅ ጋዜል ሻርማህድ በኤክስ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት ፣ አባቷ ስለ መገደሉ ማረጋገጫ በመጠየቅ በአስቸኳይ ይመለስ ስትል ጠይቃለች።
መድረክ / ፎረም