የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በተመድ እና የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ለጉቴሬዥ አቀባበል ያደረጉት ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ በቀጠናዊና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩ በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባጋሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
ጉቴሬዥ በተጨማሪም ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋራ ተነጋግረዋል።
በሠላምና ፀጥታ፣ በዘላቂ ልማት እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ባሉ ተግዳሮቶችና ልምዶች ላይ መነጋገራቸውን ሙሳ ፋኪ ማሃማት አስታውቀዋል።
መድረክ / ፎረም