ዩክሬይን ከሩሲያ አስለቅቃ ከተቆጣጠረቻት ከሰሜን ምስራቃዊዋ የካርኪቭ ከተማ በብዙ ሺዎች የተቆጠሩ ነዋሪዎችን በማስወጣት ላይ መሆኗን ዛሬ ዓርብ ገለጸች።
ዩክሬይን ሩሲያ ወረራውን ከከፈተችባት ከስድስት ወራት በኋላ ካርኪቭን አስለቅቃ ተቆጣጥራታለች።
በሰሜን ምስራቅ ካርኪቭ ክፍለ ግዛት የምትገኘው ቁልፍ የባቡር መስመር ከተማ ኩፒያንስክ ባለፉት ጥቂት ወራት በሞስኮ ኅይሎች በመድፍ እየተደበደበች ስትሆን የሞስኮ ኅይሎች ከከተማዋ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
የክፍለ ግዛቷ አስተዳዳሪ ያለማቋረጥ በሚደርሰው ድብደባ የተነሳ ለከተማዋ "የኤሊክትሪክም ሆነ የውሃ አቅርቦት ዋስትና ልንሰጥ አንችልም" በማለት ማክሰኞ እለት አስጠንቅቀው ነበር።
መድረክ / ፎረም