በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት የቀረበባችውን ክስ አስተባበሉ


ፎቶ ፋይል፦ የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ
ፎቶ ፋይል፦ የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ

የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ ሙስናን ጨምሮ ፈፀሙ በተባለው ወንጀል ዛሬ በሃገሪቱ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት ቀርበው ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።

ምክትል ፕሬዝደንቱ “በመንግሥት ላይ ለተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች ድጋፍ ሰጥተዋል፣ ሙስና ፈጽመዋል እንዲሁም በጎሳዎች መካከል ክፍፍል ለመፍጠር ሞክረዋል” የሚል ውንጀላ ቀርቦባቸዋል።

ሪጋቲ ጋቻጉዋ ክሱ ፖለቲካዊ መሆኑን አመልክተዋል። በኬንያ በወንጀል ተጠያቂ የሚሆኑ የመጀመሪያው ምክትል ፕሬዚደንት ሊያደርጋቸው ይችላል ተብሏል።

ክሱ በተጨማሪም በእርሳቸውና በፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መካከል ያለውን መልካም ያልሆነ ግንኙነት ያመለከታል ተብሏል። ሩቶ የኡሁሩ ኬንያታ ምክትል በነበሩበት ጊዜ ተመሳሳይ የሆነ አለመግባባት ውስጥ የነበሩ ሲሆን፣ ወደ ፕሬዚደንትንነት ሥልጣን ከመጡ በኋላ ተመሳሳይ ችግር እንደማይፈጠር ቃል ገብተው ነበር።

ፓርላማው ክሱን መስማት እንዲቀጥል ፍርድ ቤት በመወሰኑ፣ ፓርላማው በመስማማት ጉዳዩን ወደ ሕግ መወሰኛው ም/ቤት (ሴኔት) አስተላልፏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG