ዩናይትድ ስቴትስ ህዝባዊ ግንባር ለፍልስጤም ነጻነት (ፒኤፍኤልፒ) ለተባለው ፣ ዋሺንግተን በሽብርተኝት ለፈረጀችው ተቋም፣ ቁልፍ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማሰባሰብያ ነው ባለችው አውታር ላይ ማዕቀብ ጣለች።
የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት፣ ከካናዳ ጋር በወሰደው እርምጃ፣ ለፒኤፍኤልፒ ድርጅት "ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማሰባሰብያ ሆኖ የሚያገለግል የይስሙላ በጎ አድራጎት ድርጅት” ሲል በከሰሰው የሳሚዶውን የፍልስጤም እስረኞች አንድነት አውታረ መረብ ላይ ማዕቀብ ጥሏል።
ጋዛ ውስጥ ከእስራኤል ጋር በተደረገው ውጊያ ላይ የተሳተፈው ህዝባዊ ግንባር ለፍልስጤም ነጻነት የውጭ አሸባሪ ድርጅት እንዲሁም እና በልዩ ሁኔታ የተበየነ ዓለም አቀፍ አሸባሪ በሚል በጥቅምት 1997 እና በጥቅምት 2001 ዓመተ ምህረት በዩናይትድ ስቴትስ ተፈርጇል።
የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤቱ “ፒኤፍኤልፒ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ ገንዘብ ለማሰባሰብ ሳሚዶን አውታርን ይጠቀማል” ብሏል። የቡድኑ እንቅስቃሴ ባለፈው ዓመት በጀርመን ታግዶ ነበር።
“እንደ ሳሚዶን ያሉ ድርጅቶች ለተቸገሩት ሰብዓዊ ድጋፍ እናደርጋለን የሚሉ የበጎ አድራጎት ተቋማት ቢመስሉም ፣በእጅጉ አስፈላጊ የሆነውን የገንዘብ ድጋፍ አሸባሪዎችን ለማገዝ ያውሉታል" ሲሉ፣ የግምጃ ቤቱ የሽብርተኝነት እና ፋይናንስ ደህንነት ተጠባባቂ ጸሐፊ ብራድሊ ስሚዝ በመግለጫቸው ላይ አስታውቀዋል።
የሳሚዶን የፍልስጤም እስረኞች አንድነት አውታረ መረብ አስተያየት እንዲሰጥ ከሮይተርስ ላቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም ።
መድረክ / ፎረም