በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬኒያ ከፍተኛ ፍ/ቤት የምክትል ፕሬዝዳንቱን ክስ ክርክር ለማስቆም የቀረበ አቤቱታን ውድቅ አደረገ


የኬኒያ ምክትል ፕሬዚደንት ከስልጣን የሚያስወግድ ክስ እንዲቀርብባቸው በሚጠይቀው ረቂቅ ውሳኔ ላይ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ እንዳይከራከር ጠበቆቻቸው ያቀረቡት አቤቱታ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ፡፡

የኬኒያ የሕግ መምሪያው ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንቱ ሪጋቲ ጋቻጓ ከስልጣን እንዲወገዱ ባለፈው ሳምንት ድምጹን ሰጥቷል፡፡

የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዳኛ ቻቻ ምዊታ ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥቱ ባለው ስልጣን መሠረት ፍርድ ቤት ጣልቃ ሳይገባበት ሂደቱን መቀጠል ይችላል ሲሉ ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡

የሕግ መምሪያው ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንቱ ከሥልጣን እንዲወገዱ የሚጠይቀውን ውሳኔ በ281 ድጋፍ እና በ44 ተቃውሞ አሳልፎ ወደመወሰኛው ምክር ቤት የመራው ሲሆን መወሰኛው ነገ ረቡዕ ሊከራከር ቀጠሮ ይዟል፡፡

የኬኒያው ምክትል ፕሬዚደንት ጋቻጓ ባለፈው ሰኔ ወር የተካሄዱትን የተቃውሞ ሰልፎች ደግፈዋል፡ የተለያዩ የሙስና አድራጎቶች እና ጣፋቶች ፈጽመዋል ተብለው ተወንጅለዋል፡፡ እርሳቸው ሁሉንም ክሶች አስተባብለዋል፡፡

በኬኒያ ሕገ መንግስት መሠረት ከስልጣን የሚያስወገድ ክስ በሁለቱም ምክር ቤቶች ከጸደቀ ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ምክትል ፕሬዚደንቱ ውሳኔውን በመቃወም በፍርድ ቤት መከራከር ይችላሉ፡፡ እንደሚከራከሩም ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG