በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በከባድ ዝናብና አውሎነፋስ የተጎዱ የፍሎሪዳ አካባቢዎችን ይጎበኛሉ


ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፍሎሪዳ የባህር ዳርቻ በከባድ ዝናብና አውሎነፋስ (ሃሪኬን ሚልተን) የደረሰውን ጉዳት ለመቃኘት ሲነሱ እኤአ ጥቅምት 13 2024
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፍሎሪዳ የባህር ዳርቻ በከባድ ዝናብና አውሎነፋስ (ሃሪኬን ሚልተን) የደረሰውን ጉዳት ለመቃኘት ሲነሱ እኤአ ጥቅምት 13 2024

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፍሎሪዳ የባህር ዳርቻ በከባድ ዝናብና አውሎነፋስ (ሃሪኬን ሚልተን) የደረሰውን ጉዳት ለመቃኘት እና ምክር ቤቱ ተጨማሪ አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ ለመገፋፋት ዛሬ እሁድ ወደ አካባቢው አምርተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ማይክ ጆንሰን ጉዳዩ እኤአ ከህዳር 5 ምርጫ በኋላ እንደሚስተናገድ ቢናገሩም ወደ ቅዱስ ፒትስበርግ ከተማ የተጓዙት ባይደን የአደጋ ጊዜው እርዳታ ከወዲሁ በአስቸኳይ እንዲጸድቅ ግፊት እያደረጉባቸው ነው፡፡

ባይደን የ 612 ሚሊዮን ዶላር የኃይል ምንጭ ማቋቋሚያ ፕሮጄክቶችን ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ ይህ ድጋፍ ጉዳት የደረሰበትን የፍሎሪዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማሻሻል የሚውለውን $ 94 ሚሊዮን ዶላር ይጨምራል፡፡

ምክትል ፕሬዘዳንት ሃሪስ በሰሜን ካሮላይና ውስጥ የሚያደርጉትን የምርጫ ዘመቻ ለሁለተኛ ቀን ቀጥለዋል፡፡ ቀደም ሲል በመጀመሪያው የሃሊን አውሎ ነፋስና ከባድ ዝናብ በተጎዳው አካባቢ በሚገኘው የጥቁሮች ቤተክርስቲያንም ይገኛሉ፡፡

ዶናልድ ትረምፕ የባይደን አስተዳደር ለከባድ አውሎ ነፋሱ አደጋ በተለይም በሰሜን ካሮላይና ግዛት የሰጠውን ምላሽ ተችተውታል፡፡

ባይደን እና ሃሪስ ስለ እርዳታው የውሸት መረጃዎችን አሰራጭተዋል ሲሉ ትረምፕን ከሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG