በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና ጦር በታይዋን አቅራቢያ ለጦርነት እየተዘጀጋ መሆኑን አሳየ


ታይዋን ውስጥ እኤአ ጥቅምት 12/ 2024 በታይፔ፣በቺያንግ ካይ-ሼክ መታሰቢያ አዳራሽ ፊት ለፊት በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የክብር ዘብ አባላት የታይዋንን ሰንደቅ ዓላማ ሲያወርዱ፡፡
ታይዋን ውስጥ እኤአ ጥቅምት 12/ 2024 በታይፔ፣በቺያንግ ካይ-ሼክ መታሰቢያ አዳራሽ ፊት ለፊት በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የክብር ዘብ አባላት የታይዋንን ሰንደቅ ዓላማ ሲያወርዱ፡፡

ታይዋን የቻይና አውሮፕላን ተሸካሚው የባህር ኃይል መርከብ ቡድን ዛሬ እሁድ ወደ ደሴቲቱ ደቡባዊ አቅጣጫ መቅዘፉን አስታውቃለች፡፡ የቻይና ጦርም ዛሬ ባወጣው የቪዲዮ መልዕክት “ለውጊያ እየተዘጋጀ መሆኑን” አስታውቋል፡፡

“ትኩረቱ ታይዋን ላይ መሆኑን ያመላከተ ነው” የተባለው የቻይና ጦር ያሰራጨው የቪዲዮ ምስል የጦር መርከቦችን፣ ተዋጊ ጄቶችን፣ ሚሳይል ማስወንጨፊያዎችን እና የባህር ሰርጓጅ ተሽከርካሪዎችን አሳይቷል፡፡

ራስ ገዟ ታይዋንን የራሷ ግዛት አድርጋ የምትመለከተው ቻይና “ተገንጣይ” ስትል የምትፈርጃቸውን የታይዋን ፕሬዝዳንት ቺንግ-ቴን ትቃወማለች፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሳምንት በታይዋን የብሄራዊ ቀን ላይ ባሰሙት ንግግር “ቻይና ታይዋንን በምንም መልኩ የመወከል መብት እንደሌላት” ገልጸዋል፡፡ ደሴቲቱ “እንደ አየር ንብረት በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ብቻ ከቤጂኒግ ጋር አብራ ለመስራት ፈቃደኛ መሆንዋን” ተናግረዋል፡፡

የታይዋን መንግሥት "የደሴቲቱን የወደፊት እጣ የሚወስኑት የታይዋን ዜጎች ብቻ ናቸው" ብሏል ፡፡

የቻይና መገናኛ ብዙሃን ይህ የፕሬዚዳንቱ ንግግር የሁለቱን ግንኙነት በቀጥታ የሚጎዳ ነው ሲል የቻይና ጦርም እንደ ወትሮው ሁሉ በደሴቲቱ ዙሪያ ማንዣባቡን ይዟል፡፡

የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ እና የቻይናን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በንቃት በመጠበቅ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የቻይና ንግድ ሚኒስቴር በቅርቡ ታይዋን ላይ ተጨማሪ የንግድ ማዕቀብ እንደሚጥል አስፈራርቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG