በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ሰራተኞች በሱዳን ዜጎች በአስከፊ ሰቆቃ ውስጥ እንደሚገኙ ተናገሩ


የሱዳን እናቶች ሰቆቃ ሚያዚያ 2024
የሱዳን እናቶች ሰቆቃ ሚያዚያ 2024

የአለም አቀፉ ድንበር የለሽ ኤም.ኤስ.ኤፍ የእርዳታ ሰራተኞች አርብ ዕለት የሱዳን ህዝብ በእርስ በርስ ጦርነቱ ወደ ከፍተኛ የምግብ እጦት እያመራ በመሆኑ ከፍተኛ ቅዠት ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ተፋላሚዎቹ ወገኖች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ እንዲያደርጉ ተማጽነዋል።

ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ ከሆኑ እና በሱዳን እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ጥቂት አለም አቀፍ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የድንበር የለሽ ሀኪሞች ቡድን፤ ግጭቶች ወዳሉባቸው ስፍራዎች እጅግ የተገደበ ተደራሽነት እንዳለው ጨምሮ አስታውቋል።

በናይሮቢ በተካሄደው በዚህ መግለጫ በሱዳን ወደ ግማሽ ያህሉ ወይም 26 ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎች አስጊ የሆነ የምግብ ደህንነት ዋስትና ችግር ተጋርጦባቸዋል ሲል አስታውቋል።

የተቋሙ አስተባባሪ ክሌር ሳን ፊሊፖ “ከዚህ በኋላ እየተነጋገርን ያለነው ስለ አጣዳፊነቱ አይደለም፡ እየተናገርን ያለነው እጅግ አሰቃቂ ስለሆነው የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ነው” በማለት የጉዳቱን ጥልቀት አስረድተዋል።

ሳን ፊሊፖ የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በሰሜን ዳርፉር ዛምዛም በተሰኘ መጠለያ እና በደቡብ ዳርፉር ኒያላ የስደተኞች መጠለያዎች በሚገኙ 32 ከመቶ የሚደርሱ ሰዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መመዝገቡን አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG