መንግስት ባለፉት ስድስት አመታት ለበጎ ፍቃድ ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ይገልጻል፡፡ ይሁንና ስራዎቹ በክረምት ብቻ የሚሰሩና አብዛኛውን ህዝብ አሳታፊ በሚሆን መልኩ እየተሰሩ አይደለም በሚል ቅሬታ ይነሳል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር የወጣቶች የበጎ ፍቃድ ማስፋፊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አብይ ሃይለመለኮት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን የሚያበረታታና በተቀናጀ መልኩ ለመስራት የሚያስችል ፖሊሲ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ ፖሊሲውም በቅርቡ ይጸድቃል ብለው እንደሚጠበቅም ሃላፊው ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡
መድረክ / ፎረም