በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሞኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የኑሮ ውድነትን ሊያባብስ ይችላል ሲሉ ነዋሪዎች ስጋታቸውን ገለፁ


አዲስ አበባ
አዲስ አበባ
የሰሞኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የኑሮ ውድነትን ሊያባብስ ይችላል ሲሉ ነዋሪዎች ስጋታቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:13 0:00

በኢትዮጵያ የተደረገው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ፣ የዋጋ ግሽበቱን በማናር የኑሮ ውድነትን ያባብሳል ሲሉ ፣ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና አሽከርካሪዎች ስጋታቸውን ገልፀዋል።

በነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ዙርያ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ አሽከርካሪዎች፣ እርምጃው በስራችን ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል፣ የኑሮ ውድነትም ያባብሳል ብለዋል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በበኩሉ፣ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ መጨመርና በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ በነዳጅ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ለማድረግ መንስኤ ናቸው ሲል ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡

የተደረገው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪም ከዚህ ቀደም የተለመደ፣ የህብረተሰቡን አቅም ያገናዘበ እና ፍትሀዊ ነው በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG