በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል ግጭቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ


የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መዲና ባህር ዳር ከተማ
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መዲና ባህር ዳር ከተማ
በአማራ ክልል ግጭቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:53 0:00

በፋኖ ታጣቂ ቡድን ላይ ከፍተኛ ጥቃት ሊፈጽም መሆኑን መንግስት ባወጀበት ወቅት በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው ውጊያ ተባብሶ መቀጠሉን በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ያሉ ነዋሪዎች ገለጹ።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ የፈረስ ቤት ከተማ እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ቀራኒዮ ከተማ ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎች ከከተሞቹ ዳርቻ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ ማርፈዱን ጨምረው አመልክተዋል::

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህርዳር ከተማ ባለፈው ሳምንት የአድቬንቲስት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች የደረሱ የቦምብ ፍንዳታዎች ከፍተኛ ስጋት እንዳሳደሩባቸው የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በሰጡት መግለጫ “ሁሉም አካላት” በሰላማዊ ሰዎች እና በሲቪል ተቋማት ላይ ከማነጣጠር እንዲቆጠቡ ሲሉ ጥሪ አሰምተዋል።

በመንግስት ሰራተኞች፣ በፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ በጋዜጠኞች እና በሲቪል ማህበረሰብ አባላት ላይ እየተፈጸሙ ያሉትን የዘፈቀደ እስሮች ጉዳይ ኮምሽኑ እየተከታተለ አመልክተዋል።

በአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢዎች የተጠናቀረውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ያቀርበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG