ሩሲያ ትላንት አርብ እንዳስታወቀችው አፍጋኒስታንን እየመራ ያለው ታሊባን ከሞስኮ የአሸባሪ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ እንዲሰረዝ "ዋናው ውሳኔ" አስቀድሞ ተላልፏል ብላለች፡፡
የደቡብ እስያ ሃገራት የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ልዑክ ዛሚር ካቡሎቭ በመንግስት የሚተዳደረው የዜና ወኪል ላይ እንደገለጡት “የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲዎች የታሊባን ከፌዴራል ህጎች ጋር በተጣጣመ መልኩ መሰረዙን በተመለከተ “ህጋዊ ስራዎችን እያጠናቀቁ ነው” ብለዋል ። የመጨረሻው ውሳኔም በቅርቡ ይፋ ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡
ይህ አስተያየት የተሰማው ሞስኮ በአፍጋኒስታን ጉዳይ ለመወያየት የአካባቢው ሀገራት ጉባኤን ባዘጋጀችበት ቀን ሲሆን ውይይቱንም የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭን መርተዋል።
ከጉባኤው በኋላም ላቭሮቭ የአፍጋኒስታን የውይይቱ ተሳታፊ ልዑካናቸውን ከመሩት የታሊባን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር ካን ሙታኪ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
"ሞስኮ ከካቡል ጋር የፖለቲካ፣ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትስስር ማሳደግ ትቀጥላለች።” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ መናገራቸውም
መድረክ / ፎረም