በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩስያ ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 93 ዩክሬናውያን የጦር እስረኞች መግደሏን ኬቭ አስታወቀች 


በዩክሬን በአዞቭ ብርጌድ ውስጥ ያሉ ወታደሮች በባልደረባቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ፣ መስከረም 24፣ 2017 ዓ.ም
በዩክሬን በአዞቭ ብርጌድ ውስጥ ያሉ ወታደሮች በባልደረባቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ፣ መስከረም 24፣ 2017 ዓ.ም

ከሩሲያ የዩክሬን ወረራ ጋር በተያያዘ የጦር ወንጀሎችን ለመመርመር ኃላፊነት የተሰጠው የህግ አስከባሪ ባለስልጣን 93 የዩክሬን የጦር እስረኞችን መገደል ጋር የተያያዙ ማስረጃዎችን መመዝገቡን አስታውቋል፡፡

በትጥቅ ግጭት ውስጥ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ለመመርመር የተቋቋመው የዩክሬን ዐቃቤ ህግ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ዲፓርትመንትን የሚመሩት ዩሪ ቤሎሶቭ ትላንት በቴሌቪዥን ባቀረቡት የቅርብ ጊዜ መረጃ “አሁን በጦር ሜዳ የተገደሉት የ93 ወታደሮቻችን አሟሟት በተመለከተ መረጃ አግኝተናል” ብለዋል፡፡

ሰማንያ በመቶ ግድያ የተመዘገበውም በዚህ አመት ነው ብለዋል፡፡ በጽህፈት ቤቱ የቴሌግራም ቻናል ላይ በወጣ ይፋዊ መግለጫ መሠረት የሩሲያ ኃይሎች በዶኔትስክ ክልል ውስጥ በማይኮላይቪካ እና በሱኪይ ያር መንደሮች አቅራቢያ 16 የዩክሬን “የጦርነት እስረኞችን” ገድለዋል ።

በተለያዩ የቴሌግራም ቻናሎች የተሰራጨው የተንቀሳቃሽ ምስል በቅርቡ የዩክሬን ወታደሮች በሩሲያ ወታደሮች ተይዘው ከጫካ አካባቢ ሲወጡ ና የሩሲያ ኃይሎችም በእስረኛ ወታደሮች ላይ ተኩስ ሲከፍቱ ያሳያል፡፡ ምስሉ በገለልተኛ አካል አልተጣራም፡፡፡

በአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ መሰረት እጃቸውን የሰጡ ወታደሮችን መግደል እንደ የጦር ወንጀል ይቆጠራል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG