በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት ፓርላማው ተጠያቂ ሊያደርጋቸው የጀመረው ሂደት እንዲቆም ጠየቁ


የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ
የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ

የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ ፈፀሙ ላተባለው ጥፋት ፓርላማው ተጠያቂ እንዲሆኑ የጀመረው ሂደት እንዲቋረጥ የሚጠይቅ አቤቱታ፣ ሐሙስ ዕለት ናይሮቢ ለሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስገብተዋል።

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አጋሮች፤ ጋቻጉዋ በጎሳዎች መካከል ጥላቻ ቀስቅሰዋል፣ መንግስት ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል እንዲሁም ምንጩ የማይታወቅ ንብረት አካብተዋል ሲሉ ሐሙስ ዕለት ለፓርማው ሃሳብ አቅርበዋል።

ጋቻጉዋ በበኩላቸው ከሂደቱ እንዲገለሉ መደረጋቸውን ገልጸው፣ በዓመቱ መጀመሪያ ከተካሄዱ ጸረ-መንግስት ተቃውሞዎች ጀርባ እሳቸው እንዳሉ ተደርጎ በሩቶ አጋሮች የቀረበባቸውን ክስ አስተባብለዋል።

ጉቻጉዋ፤ የቀረበባቸው ክስ "የኬንያ ህዝብ እ.አ.አ በነሐሴ 2022 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ያሳየውን ሉዓላዊ ውሳኔ ለማክሸፍ የተቀነባበረ የፖለቲካ ደቦ" ነው ማለታቸውን ለፍርድቤት ያስገቡት እና ሮይተርስ የተመለከተው ማመልከቻ ያሳያል።

ጋቻጉዋ ከፍተኛ የህዝብ ድምፅ በማሰባሰብ ሩቶ ምርጫ እንዲያሸንፉ አግዘው የነበረ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሁለቱ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ተዘግቧል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱን ተጠያቂ ለማድረግ የሚካሄደው ሂደት ዓርብ ዕለት እንደሚጀምር ዕቅድ የተያዘለት ሲሆን፣ በሚቀጥለው ሳምንት ፓርላማ ቀርበው ለክሶቹ ምላሽ እንደሚሰጡም ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG