በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን  ወደ እስራኤል ሚሳኤል ማስወንጨፏ ቀጣናውን ወደ ባሰ ትርምስ የሚከት እንደሆነ ተገለጸ


ኢራን ትናንት ከ180 በላይ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ካስወነጨፈች በኋላ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል።

በውጭ ጉዳይ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግኑኝነት ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ተመራማሪ ዶ/ር ዳር እስከዳር ታየ ኢራን በዋና አጋሯ ሂዝቦላ ላይ እስራኤል የወሰደችው ከባድ ወታደራዊ ርምጃ ሚሳኤል ለማስወንጨፏ ዋና ምክንያት ነው ይላሉ::

ይህ የቀጣናው ትርምስ ወደ ተባባሰ ሁኔታ ለመግባቱ መጀመርያ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው ያሉት ዶክተር ዳር እስከዳር እስራኤል ለጥቃቱ የምትሰጠው ምላሽም ቀጣይ ሁኔታውን የሚወስን ይሆናል ብለዋል::

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG