በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን  ወደ እስራኤል ሚሳኤል ማስወንጨፏ ቀጣናውን ወደ ባሰ ትርምስ ይከተዋል - የዲፕሎማሲና አለም አቀፍ ግኑኝነት ተመራማሪ


ኢራን ትናንት 180 ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ካስወነጨፈች በኋላ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል።
በውጭ ጉዳይ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግኑኝነት ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ተመራማሪ ዶ/ር ዳር እስከዳር ታየ ኢራን በዋና አጋሯ ሂዝቦላ ላይ እስራኤል የወሰደችው ከባድ ወታደራዊ ርምጃ ሚሳኤል ለማስወንጨፏ ዋና ምክንያት ነው ይላሉ::

ይህ የቀጣናው ትርምስ ወደ ተባባሰ ሁኔታ ለመግባቱ መጀመርያ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው ያሉት ዶክተር ዳር እስከዳር እስራኤል ለጥቃቱ የምትሰጠው ምላሽም ቀጣይ ሁኔታውን የሚወስን ይሆናል ብለዋል::

አስማማው አየነው ነው ያነጋገራቸው፡፡

XS
SM
MD
LG