በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ የዚምባቡዌ እና የሌሎች ሀገራት ማዕቅብ እንዲነሳ ጠየቀች


የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ
የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ዛሬ በመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር በዚምባቡዌ፣ ቬንዙዌላ እና ኩባ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች እንዲነሱ ጠየቁ፡፡ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም በጎርጎሮሳዊያኑ 2009 በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቅብ አእስመልክተው ‘የበላይነት የተጠናወታቸው ሃይሎች’ እና ‘የማይረባ ፖሊሲ የሚከተሉ አሃዳዊ የአለም ስርዓት አመራሮች’ ሲሉ የጠሯቸውን ከሰዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ የተጠቀሱት ሦስቱ ሀገራት የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ሙስና እና ምርጫን በማደናቀፍ በዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ የተጣለባቸው ናቸው፡፡ ኩባ በአሜርካ ሽብርተኝነት ከሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚዋ ስትሆን ለብዙ አስርት ዓመታት የዘለቀ ማዕቀብ የተጣለባት ሀገር ናት፡፡

በተመሳሳይ ኤርትራም በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰውን አልሻባብ የሽብር ቡድን በመደገፍ በሚል ማዕቀብ ተጥሎባት የነበረ ቢሆንምእኤአ በ2018 ማዕቀቡ ተንስቶላታል፡፡ ኤርትራ ክሱን አልተቀበለችም፡፡

በንግግራቸው ማዕቀቡን ያነሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ “ምንም እንኳን የኤርትራ ማዕቅብ በጎርጎርሳዊያኑ 2018 ቢነሳም፤ ጥያቄው ግን ቀድሞውንም ለምን ተጣለ? የሚለው ነው” ብለዋል፡፡

ኦስማን በዚምባቡዌ፣ ቬንሱዌላ እና ኩባ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ‘ፍትሃዊ አይደለም’ ሲሉ እንዲነሳ ጠይቀዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG