በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ሶሪያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት 37 ታጣቂዎች ተገደሉ


ሶሪያ
ሶሪያ

ዩናይትድ ስቴትስ በሶሪያ ታጣቂዎች ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ከአልቃይዳ እና እስላማዊ መንግሥት (አይ ኤስ) የሽብር ቡድን ጋር ግንኙት ያላቸው 37 ታጣቂዎችን መግደሏን የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አስታወቀ።

ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች እንደነበሩ ተገልጿል።

ባለፈው ማክሰኞ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ በፈጸመው ጥቃት፤ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው ሁራስ አል-ዲን ቡድንንና ሌሎች ስምንት ከፍተኛ ታጣቂዎች ዒላማ አድርጓል ሲል አስታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ በኩርዶች ለሚመሩት የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ድርጅትና ቁልፍ አጋሮቻቸው ምክር እና እገዛ ያደርጋሉ።

በተጨማሪም በሶሪያ የአይ ኤስ የሽብር ቡድን ማንሰራራትን ለመከላከል 900 የሚደርሱ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች በአካባቢው ይገኛሉ።

አካባቢው ከኢራቅ ጋር ቁልፍ የሆነ የድንበር መሻገሪያን ጨምሮ በኢራን የሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች የሚንቀሳቀሱባቸው ስትራቴጂካዊ አካባቢዎች ናቸው፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG