በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኒው ዮርክ ከንቲባ ኤሪክ አዳምስ በሕገ ወጥ መንገድ ከውጭ የዘመቻ መዋጮ በመቀበል ወንጀል ተከሰሱ


የኒው ዮርክ ከንቲባ ኤሪክ አዳምስ
የኒው ዮርክ ከንቲባ ኤሪክ አዳምስ

የኒው ዮርክ ከንቲባ ኤሪክ አዳምስ ከውጭ ሀገር ምንጮች ሕገ ወጥ የምርጫ ዘመቻ መዋጮ በመቀበል ወንጀል ክስ እንደቀረበባቸው ተዘገበ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የኒው ዮርክ ማንሃተን አቃቤ ሕግ ቢሮ በከፈተው የክስ ዶሴ ከንቲባው ከተማዋ ለዘመቻ በሚሰጡ አነስተኛ መዋጮዎች መጠን ተጨማሪ ገንዘብ ለመስጠት ያወጣችውን መርሐ ግብር በሚቀበሉት ሕገ ወጥ መዋጮ ያለአግባብ ተጠቅመውበታል ሲል ወንጅሏቸዋል፡፡

ከንቲባው ማንሃተን የሚገኘውን የቱርክ ቆንስላ በሚመለከቱ ደንቦች ዙሪያ እርዳታ ከጠየቋቸው የቱርክ ባለስልጣኖች እጅግ ቅንጡ የሆኑ ጉዞዎች በነጻ ወይም በከፍተኛ ቅናሽ ለማግኘት በቀጥታ መጠየቅ አለያም እንዲሰጣቸው ማግባባት ጨምሮ ጉቦ በመቀበል ተወንጅለዋል፡፡

ክሱ በይፋ ከመከፈቱ አስቀድሞ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ወኪሎች ዛሬ ማለዳ ከንቲባው መኖሪያ ቤት ገብተው ስልካቸውን ወርሰዋል፡፡

ከንቲባ አዳምስ ትላንት ረቡዕ ማታ በቪዲዮ በተቀዳ መግለጫቸው በሀሰት የተመሰረተብኝን ክስ እታገላለሁ ብለዋል፡፡ ከንቲባውን ከስራ የማባረር ሥልጣን ያላቸው የኒው ዮርክ ግዛት አገረ ገዢ ካቲ ሆከል ቃል አቀባይ ባወጡት መግለጫ አገረ ገዢዋ አሳሳቢ የሆኑትን ዜናዎች ሰምተዋል፡፡ ሁኔታውን በመከታተል ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG