በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ12ኛ ክፍል ፈተና ለተገኘው አስደንጋጭ ውጤት ተጠያቂው ማነው?

በ12ኛ ክፍል ፈተና ለተገኘው አስደንጋጭ ውጤት ተጠያቂው ማነው?
በ12ኛ ክፍል ፈተና ለተገኘው አስደንጋጭ ውጤት ተጠያቂው ማነው?
በ12ኛ ክፍል ፈተና ለተገኘው አስደንጋጭ ውጤት ተጠያቂው ማነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:01 0:00

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ 674 ሺህ 823 ተፈታኞች ውስጥ 5.4 ከመቶ ብቻ ማለፋቸው እጅግ በጣም እንዳስደነገጣቸው እና እንዳሳዘናቸው ተማሪዎች እና መምህራን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ላለፉት ሦስት ተከታታይ አመታት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት የቻሉት ተማሪዎች ቁጥር እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑ በተማሪዎቹ የወደፊት እጣ ፈንታ እና በሀገሪቱ ላይ የሚፈጥረው ጫና እጅግ እንደሚያሳስባቸውም ገልጸዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው ውጤቱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ዘንድሮ ካለፉት ሁለት አመታት የተሻለ ውጤት መመዝገቡን አመልክተው "ከሥር መሠረቱ የተበላሸ" ያሉትን የትምህርት ስርዓት ለማስተካከል ግን ጊዜ እንደሚወስድ ተናግረዋል።

(ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ)

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG